July 29, 2025 ችግኝ ተከላ ተካሄደ ዛሬ የምንተከለውን ችግኝ፤ ነገም በመንከባከብ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ዛሬ የምንተከለውን ችግኝ፤ ነገም በመንከባከብ ኃላፊነታችንን እንወጣለን አቶ ሰብስብ ሁሴን የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን አመራሮች፣ ሰራተኞቸና ባለድረሻ አካላት በዛሬው ዕለት በጉለሌ የሙስሊሞች መቃብር ግቢ ውስጥ ባለው የወንዝ ዳርቻ በመትከል ማንሰራራት! በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡ የችግኝ ተከላው ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን፤ ዛሬ ከመትከል ባለፈ፤ ነገ የተከልናቸውን ችግኞች በመንከባከብ የሚጠበቅብንን የትውልድ አደራ በመወጣት ፀድቆ ለፍሬ እንዲበቃ የማድረግ ስራ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ በመትከል ማንሰራራት! በሚል መሪ ቃል 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር ለመትከል በተያዘው ዕቅድ ውስጥ ሁሉም በንቃት በመሳተፍ ሀገራዊ ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡ የችግኝ ተከላው ተሳታፊዎች የአረንጓዴ አሻራ ለትውልድ የሚቀመጥ በመሆኑ በተጀመረው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ላይ በማሳተፍና በቀጣይ ችግኞቹ በአግባቡ እንዲፀድቁ የመንከባከብ ስራ እንደሚያከናውኑ ቃል ገብተዋል፡፡ አክለውም ዛሬ የተከልነው ችግኝ፤ ውጤቱ ለነገ የሚተርፍ መሆኑን አንስተው የምንተክላቸው ችግኞች እንደ ሀገር የነበረውን የአረንጓዴ ሽፋን መጠንን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የሚያበረክተው አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡ እንዲሁም ለምግብነት ሊውሉ የሚችሉ ችግኞችን በመትከል ረገድ እንደ ሀገር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልፀዋል፡፡